ዘዳግም 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤትህ ደጃፍ መቃኖችና በቅጽር በሮችህ ላይ ጻፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤትህ መቃኖችና በግቢህም በሮች ላይ ጻፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤትህም መቃኖች፥ በቅጽርህም በሮች ላይ ጻፈው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤትህም መቃኖች፥ በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። |
እግዚአብሔር “አሁን ሄደህ ይህ ነገር ለሚመጡት ዘመናት ቋሚ ምስክር ይሆን ዘንድ እነርሱ እያዩ በሰሌዳ ላይ ቅረጸው፤ በመጽሐፍም ጻፈው” አለኝ።
ከበራችሁና ከመቃኖቹ በስተጀርባ የጣዖት ምስሎችን አስቀምጣችኋል፤ እኔን ትታችሁ ዝሙት ለመፈጸም ወደ አልጋዎቻችሁ ወጥታችኋል፤ በዝሙት ዋጋ ተደራድራችሁ ፍትወታችሁን ታረካላችሁ።
“እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር በልቡናችሁና በአእምሮአችሁ ቅረጹአቸው፤ መታሰቢያም ይሆኑላችሁ ዘንድ እነርሱን በክንዳችሁ ላይ እሰሩ፤ በግንባራችሁም ላይ እንደማስታወሻ አኑሩአቸው፤