ዘዳግም 5:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ አላችሁ፦ ‘በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር በሰማነው ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ታላቅነቱንና ክብሩን በግልጥ አሳይቶናል፤ እግዚአብሔር ካነጋገረው በኋላ እንኳ ሰው በሕይወት መኖር እንደሚችል በዛሬው ዕለት አይተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላችሁ፤ “አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ግርማውን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እግዚአብሔር አነጋግሮትም እንኳ፣ ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አላችሁ፦ ‘እነሆ፥ አምላካችን ጌታ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔር ከሰው ተነጋግሮ ሰውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም መካከል ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር፥ ሰውዬው በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውዬውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። |
የሆነውን ሁሉ በዚህ ምድር ለሚኖሩት ሕዝቦች ይነግራሉ፤ እነዚህ ሕዝቦች አንተ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆንህንና ደመናህ በላያችን በረበበ ጊዜ በግልጥ እንደምትታይ፥ ቀን በደመና ዐምድ፥ ሌሊት በእሳት ዐምድ እፊት እፊታችን እየሄድክ እንደምትመራን ከሰሙ ቈይተዋል።