ዘዳግም 4:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ በስተምሥራቅ ሦስት ከተሞች በመለየት ከለለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሙሴ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞች በመለየት ከለለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ሙሴ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞችን ለየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ሙሴ ትናንት ከትናንት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይሸሽባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች ለየ። |
“እግዚአብሔር አምላክህ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ለአንተ በተሰጠው ድርሻና በጐረቤትህ መካከል በቀድሞ ትውልድ የተተከለውን የድንበር ምልክት አታፍርስ።
አምላክህ እግዚአብሔር እንድትኖርባት የሚሰጥህን ምድር ለሦስት ትከፍልና በያንዳንዱ ክፍል አንዳንድ ከተማ የተለየ ታደርጋለህ፤ ነፍሰ ገዳይም ይሸሽባቸው ዘንድ ወደ እነዚያ የሚወስዱትን መንገዶች ታዘጋጃለህ፤ ከዚያ በኋላ አንድ ነፍሰ ገዳይ ሕይወቱን ለማትረፍ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ ይሂድ፤
ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ ጠላትነት ሳይኖረው ባለማወቅ ማንኛውንም ሰው የገደለ ሕይወቱን ለማትረፍ ወደዚያ ሄዶ ማምለጥ እንዲችል ነው፤ አምልጦም ከእነዚህ ከተማዎች ወደ አንዲቱ ከገባ ሕይወቱን ያድናል።