ዘዳግም 4:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ለእግዚአብሔር አምላካችሁ ታማኞች በመሆን ስለ ጸናችሁ ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት ትኖራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁን እግዚአብሔርን የተከተላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት አላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን ጌታ አምላካችሁን የተከተላችሁ ሁላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት ትኖራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግን አምላካችሁን እግዚአብሔርን የተከተላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ ሁላችሁ በሕይወት ትኖራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን አምላካችሁን እግዚአብሔርን የተከተላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ ሁላችሁ በሕይወት ትኖራላችሁ። |
“በመላዋ ኢየሩሳሌም ከተማ ተዘዋወር፤ በከተማይቱ ከተፈጸመውም አጸያፊና አሳፋሪ ነገር የተነሣ በመሠቀቅ ባዘኑት ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት አድርግባቸው!” አለው።
እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።
አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉት፤ እርሱን ብቻ ፍሩ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ቃሉንም ስሙ፤ እርሱንም አምልኩ፤ ከእርሱም ጋር ያላችሁ አንድነት የጠበቀ ይሁን።
አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።”
በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።
ሙሴ የሰጣችሁን ሕግና ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ውደዱ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ለእርሱም ታማኞች ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ፥ በፍጹም ሐሳባችሁ አገልግሉት።”
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።
ከዚህ በኋላ ዙፋኖችን አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው አየሁ፤ ስለ ኢየሱስ በመመስከራቸውና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሶች አየሁ፤ እነርሱ ለአውሬውና ለምስሉ ያልሰገዱ፥ ምልክቱንም በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያላደረጉ ናቸው፤ እነርሱ ከሞት ተነሥተው ከክርስቶስ ጋር ሺህ ዓመት ነገሡ።