ዘዳግም 4:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረጉ ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ከእናንተ የሚበልጡትንና ኀያላን የሆኑትን ሕዝቦች አስወጥቶ ምድራቸውን ለእናንተ ርስት ለማድረግ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግብፅ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆቹን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ |
አንተ አምላካችን ነህ፤ ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህች ምድር በገባ ጊዜ ቀደም ሲል በዚህ ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አስወጥተህ ወዳጅህ ለነበረው ለአብርሃም ዘሮች ምድሪቱን የሰጠህ አንተ ነህ፤
ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር እነዚህን በፊታችሁ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያስወጣል፤ እናንተም በብዛትና በኀይል ከእናንተ እጅግ ብርቱዎች የሆኑትን ሕዝቦች ምድር ትወርሳላችሁ።
“ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ ‘ተመልከት እኔ ንጉሥ ሲሖንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ አሁን ድል በማድረግ ምድሩን ወርሰህ ስፈርበት።’
“እግዚአብሔር አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህ ጊዜ በፊትህ ያሉትን ብዙ ሕዝቦች ያስወግድልሃል፤ እነርሱም ከአንተ በብዛትና በኀይል የሚበልጡት ሰባት የአሕዛብ ነገዶች ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
ኢያሱም ንግግሩን በመቀጠል፦ “ሕያው እግዚአብሔር በመካከላችሁ መሆኑን የምታውቁት እናንተ ወደ ፊት እየገፋችሁ በሄዳችሁ መጠን እርሱ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ሒዋውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ የሚያስወጣ በመሆኑ ነው።