ዘዳግም 33:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ጋድ ነገድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት ያሰፋ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ጋድ ክንድን ወይም ግንባርን ለመስበር፥ እንደ አንበሳ ያደባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተመሰገነ ነው! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፣ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ጋድም እንዲህ አለ፥ “ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፥ እንደ አንበሳይቱ ዐርፎአል፥ ክንድንና ራስን ይቀጠቅጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦ ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፤ እንደ አንበሳ ያለቆችን ክንድ ቀጥቅጦ ያርፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ጋድም እንዲህ አለ፥ 2 ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፤ 2 እንደ አንበሳይቱ ዐርፎአል፤ 2 ክንድንና ራስን ይቀጠቅጣል። |
ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው?
ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
አንበሳ በብዙ የዱር አራዊት መካከል፥ የአንበሳ ደቦልም በበግ መንጋዎች መካከል ዘለው ጉብ እያሉባቸውና እየቦጫጨቁ በሚሄዱበት ጊዜ ለአራዊቱ ምንም ረዳት አይገኝላቸውም፤ ከሞት የተረፉትንም የያዕቆብን ልጆች በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደዚሁ ያደርጋሉ።
የሮቤልና የጋድ ነገዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በርስትነት የሰጣቸውን ምድር ቀደም ብለው ተረክበዋል። ይህም ምድር የሚገኘው በስተምሥራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ነው።