ዘዳግም 32:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ይህስ በእኔ ዘንድ የተጠበቀ፥ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔ ዘንድ ያለው ትእዛዝ ይህ አይደለምን? በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ የለምን? 2 በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? |
“እናንተና የቀድሞ አባቶቻችሁ፥ ንጉሦቻችሁና መሪዎቻችሁ፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ዕጣን ታጥኑ እንደ ነበረ፥ እግዚአብሔር አያስበውም ወይም ረስቶታል ብላችሁ ታስባላችሁን?
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
እግዚአብሔርም በብርቱ ተቈጣ፤ ከብርቱ ቊጣውም የተነሣ ከምድራቸው ነቃቅሎ ወደ ባዕድ አገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው። ስለዚህም እነሆ፥ ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’