ከእናንተ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ሁሉ፥ አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይሥራ።
ዘዳግም 32:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት የእነርሱ አምላክ እንደ እኛ አምላክ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እንደ አምላኮቻቸው አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችን እንደ አማልክቶቻቸው አይደለም፤ 2 ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው። |
ከእናንተ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ሁሉ፥ አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይሥራ።
እግዚአብሔር የሠረገላዎቻቸውን መንኰራኲሮች ከመሬት ጋር ስላጣበቀባቸው ሠረገሎቻቸውን ነድተው ማንቀሳቀስ አልቻሉም፤ ግብጻውያንም፥ “እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ረድቶ እኛን እየተዋጋን ነው፤ ስለዚህ ከፊታቸው እንሽሽ!” ተባባሉ።
ሽብር በተነሣ ጊዜ ምሽጋቸው ይፈርሳል፤ የጦር መኰንኖቻቸውም አርማቸውን ትተው በመርበድበድ ይሸሻሉ”። እሳቱ በጽዮን፥ እቶኑ በኢየሩሳሌም የሆነው እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
አደርጋለሁ ብሎ ያቀደውን ሁሉ እነሆ አሁን ፈጽሞታል፤ ይህም ሁሉ የሆነው እናንተ ኃጢአት በመሥራታችሁና ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛችሁ ምክንያት ነው።
ንጉሡም ዳንኤልን “የአንተ አምላክ ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ አምላክ ነው፤ የነገሥታት ሁሉ ጌታ ነው፥ ምሥጢርንም ሁሉ መግለጥ የሚችል ነው፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ታላቅ ምሥጢር ለመግለጥ ችለሃል” አለው።
“እንደዚህ የሚታደግ ሌላ አምላክ የለም፤ ስለዚህ በአገሮች ሁሉ በሚኖሩና ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን በሚናገሩ ሕዝቦች ሁሉ መካከል በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር ሰውነቱ ተቈራርጦ እንዲጣልና ቤቱም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን ዐውጃለሁ።”
በያዕቆብ ልጆች ላይ ምንም ዐይነት ጥንቈላ፥ በእስራኤልም ላይ ምንም ዐይነት አስማት አይሠራም፤ እነሆ፥ አሁን ለያዕቆብና ለእስራኤል፥ ‘እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ተመልከቱ!’ ይባላል።