ዘዳግም 31:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት የሚሸከሙ ሌዋውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን የኪዳን ታቦት የሚሸከሙ ሌዋውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያንን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ |
“የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ይህን መጽሐፍ ወስዳችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ምስክር ይሆንባቸዋል።
ከዚያ በኋላ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አገልጋዮች ለሆኑት ለሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሕዝብ አለቆች ሰጣቸው።