“ከላይ እሳት ላከ፤ እሳቱም ወደ አጥንታችን ዘለቀ፤ ለእግራችን መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰን፤ ሕሊናችንን አስቶ ቀኑን ሙሉ ሰውነታችን እንዲዝል አደረገ።
ዘዳግም 28:66 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕይወትህ ዘወትር በጭንቀት ላይ ይሆናል፤ የመኖር ዋስትናህም የተረጋገጠ ባለመሆኑ ቀንና ሌሊት በፍርሃት ትዋጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፣ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፣ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፥ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፥ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትህ በዐይኖችህ ፊት የተሰቀለች ትሆናለች፤ ሌሊትና ቀንም ትደነግጣለህ፤ በሕይወትህም አትታመንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍስህም ታመነታለች፤ ሌሊትና ቀንም ትፈራለህ፥ በሕይወትህም አትታመንም፤ |
“ከላይ እሳት ላከ፤ እሳቱም ወደ አጥንታችን ዘለቀ፤ ለእግራችን መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰን፤ ሕሊናችንን አስቶ ቀኑን ሙሉ ሰውነታችን እንዲዝል አደረገ።
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍትና ለእግርህ ማሳረፊያ ቦታ አይኖርህም፤ እግዚአብሔርም የባባ ልብ፥ በናፍቆት የፈዘዘ ዐይን፥ ተስፋ የቈረጠ ስሜት ይሰጥሃል።