ዘዳግም 28:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይኑን ሐረግ ትል ስለሚበላው ወይን ተክለህ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን የወይን ዘለላ ሰብስበህ አትበላም፤ ወይም ከእርሱ የወይን ጠጅ አትጠጣም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይን ትተክላለህ፤ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን ትል ይበላዋልና ዘለላውን አትሰበስብም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይን ተክለህ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን ትል ስለሚበላው ዘለላውን አትሰበስብም ወይም ከወይኑ አትጠጣም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይን ትተክላለህ፤ ታበጀውማለህ፤ ከወይኑም አትጠጣም፤ ክፉ ትልም ይበላዋልና በእርሱ ደስ አይልህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይን ትተክላለህ ታበጀውማለህ፤ ትልም ይበላዋልና ከእርሱ ምንም አትሰበስብም፥ የወይን ጠጁንም አትጠጣም። |
በሩብ ጋሻ መሬት ላይ የተተከለው የወይን ፍሬ ስምንት ሊትር የወይን ጭማቂ ብቻ ይወጣዋል፤ አንድ መቶ ሰማኒያ ኪሎ እህል የተዘራበትም የእርሻ ምርት ዐሥራ ስምንት ኪሎ ብቻ ይገኝበታል።”
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥