La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 28:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከብትህ በፊትህ፥ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ ነገር ግን ከሥጋው አትቀምስም፤ አህዮችህ በፊትህ ተስበው ይወሰዳሉ፤ ነገር ግን አይመለሱልህም፤ በጎችህ ለጠላቶችህ ተላልፈው ይሰጣሉ፤ እነርሱን ለማዳን የሚረዳህም የለም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምስም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚያስጥላቸውም አይኖርም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ አንዳች ግን አትቀምሰውም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ ለአንተም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህ ማንም አይኖርም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሬህ በፊ​ትህ ይታ​ረ​ዳል፤ ከእ​ር​ሱም አት​በ​ላም። አህ​ያህ ከእ​ጅህ በግድ ይወ​ሰ​ዳል፤ ወደ አን​ተም አይ​መ​ለ​ስም፤ በጎ​ችህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ይሰ​ጣሉ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም አታ​ገ​ኝም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሬህ በፊትህ ይታረዳል፥ ከእርሱም አትበላም፤ አህያህ ከእጅህ በግድ ይወሰዳል፥ ወደ አንተም አይመለስም፤ በግህ ለጠላቶችህ ትሰጣለች፥ የሚያድንህም አታገኝም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 28:31
8 Referencias Cruzadas  

በእግዚአብሔርም የቊጣ ቀን የቤቱ ንብረት ሁሉ በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል።


እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።


ሰብላችሁንና ምግባችሁን ሁሉ ጠራርገው ይበሉታል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ሁሉ ይገድላሉ፤ የበጎችና የከብት መንጋችሁን ሁሉ ያርዳሉ፤ የወይን ተክሎቻችሁንና የበለስ ዛፎቻችሁን ሁሉ ያጠፋሉ፤ ሠራዊታቸውም የምትተማመኑባቸውን የተመሸጉ ከተሞቻችሁን ሁሉ ያወድማሉ።


“ልጃገረድ ለማግባት ታጫለህ፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይደፍራታል፤ ቤት ትሠራለህ፤ ነገር ግን አትኖርበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ነገር ግን በፍሬው አትጠቀምበትም።


ዐይንህ እያየ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለባዕዳን ይሰጣሉ፤ የልጆችህን መመለስ በከንቱ በመጠባበቅ ዐይንህ ሲንከራተት ይኖራል፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም።


የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንደገና በደሉ፤ እግዚአብሔርም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ሙሉ ገዙአቸው፤


በአገሪቱ ላይ በመስፈር በጋዛ ዙሪያ እስካለው ስፍራ ድረስ የምድሪቱን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ የበግ፥ የከብትና የአህያ መንጋቸውንም እየነዱ ስለሚወስዱባቸው ለእስራኤላውያን ምንም ነገር አያስቀሩላቸውም ነበር።