ዘዳግም 27:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በዚያ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በዚያ ቀን እንዲህ ብሎ ሕዝቡን አዘዘ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በዚያን ቀን እንዲህ ብሎ ሕዝቡን አዘዘ፦ |
“በዚያን ጊዜ እነርሱን እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤ ‘በሕዝባችሁ መካከል የሚነሣውን የጠብና የክርክር አቤቱታ አድምጡ፤ በራሳችሁ ሕዝብ ወይም በእናንተ ውስጥ በሚኖሩት መጻተኞች መካከል ስለሚነሣው ጠብና ክርክር ሁሉ በትክክል ፍረዱ።
“ዮርዳኖስን ከተሻገራችሁ በኋላ ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው የስምዖን፥ የሌዊ፥ የይሁዳ፥ የይሳኮር፥ የዮሴፍና የብንያም ነገዶች ናቸው።
የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ ቀደም ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እስራኤላውያን ሁሉና መጻተኞች ሽማግሌዎቻቸው፥ ሹሞቻቸውና ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ከሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት ግራና ቀኝ እኩሌቶቹ ከጌሪዚም ተራራ ፊት ለፊት፥ እኩሌቶቹ ደግሞ ከኤባል ተራራ ፊት ለፊት ቆሙ።