ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ ባዕድ ሰው “እግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ይለየኛል” ብሎ አያስብ፤ ጃንደረባ የሆነ ሰው ልጅ ባለመውለዱ፦ “እንደ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።
ዘዳግም 23:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከጋብቻ ውጪ ዲቃላ ሆኖ የተወለደና የእርሱም ዘር ሆኖ የተወለደ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ገብቶ አይቈጠር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲቃላም ይሁን የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ፣ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከጋብቻ ውጪ የተወለደ ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። |
ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ ባዕድ ሰው “እግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ይለየኛል” ብሎ አያስብ፤ ጃንደረባ የሆነ ሰው ልጅ ባለመውለዱ፦ “እንደ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።
በጀርባው ላይ ጉብር ያለበት ወይም ድንክ፥ የዐይን ሕመም ወይም ልዩ ልዩ ዐይነት የቆዳ በሽታ ያለበት፥ ወይም ጃንደረባ የምግብ ቊርባን ለእኔ ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ አይገባውም።
እንግዲህ እናንተ የምትሠሩት የአባታችሁን ሥራ ነው።” እነርሱም “እኛ በምንዝር የተወለድን ዲቃላዎች አይደለንም፤ አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት።