“ወደ እዚህ ያመጡን በመጀመሪያ ጊዜ በስልቻዎቻችን ውስጥ ተመልሶ ስለ ተገኘው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም” በማለት፤ ሰዎቹ ወደ ዮሴፍ ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ “በዚህ ምክንያት ያሠቃዩናል፤ አህዮቻችንን ወስደው እኛንም የእነርሱ ባሪያዎች ያደርጉናል” ብለውም አሰቡ።
ዘዳግም 22:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልጅህን ድንግልና የሚያመለክት ማስረጃ አላገኘሁም ብሎ የልጄን ስም አጐደፈ፤ ለልጄ የድንግልናዋ ማረጋገጫ ምልክት ይኸውና!’ በማለት በመሪዎቹ ፊት የማስረጃውን ሻሽ ይዘርጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሟንም በማጥፋት፣ ‘ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም’ ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ፤” ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፦ ‘በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም’ ብሎ የነውር ነገር አወራባት፥ የልጄም ምልክት ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም የድንግልናዋ ልብስ ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም ምልክት ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። |
“ወደ እዚህ ያመጡን በመጀመሪያ ጊዜ በስልቻዎቻችን ውስጥ ተመልሶ ስለ ተገኘው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም” በማለት፤ ሰዎቹ ወደ ዮሴፍ ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ “በዚህ ምክንያት ያሠቃዩናል፤ አህዮቻችንን ወስደው እኛንም የእነርሱ ባሪያዎች ያደርጉናል” ብለውም አሰቡ።