የእኛ መሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ካህናትም መለከት ለመንፋት ተዘጋጅተው እዚህ ከእኛ ጋር ይገኛሉ፤ እነርሱ እምቢልታ መንፋት እንደ ጀመሩም እኛ በእናንተ ላይ ጦርነት እንከፍታለን፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከቶ ድል ማድረግ ስለማትችሉ፥ ከቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት አትግጠሙ!”
ዘዳግም 20:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጦርነት ከመጀመራችሁ በፊት ካህኑ ወደ ሠራዊቱ ቀርቦ እንዲህ ይበል፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፣ ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሰራዊቱ ይናገር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፥ ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሕዝቡ ይናገር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ጦርነትም በቀረባችሁ ጊዜ ካህኑ ይቅረብ፤ ለሕዝቡም እንዲህ ብሎ ይንገራቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰልፍም በቀረባችሁ ጊዜ ከህኑ ይቅረብ ለሕዝቡም እንዲህ ብሎ ይንገራቸው፦ |
የእኛ መሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ካህናትም መለከት ለመንፋት ተዘጋጅተው እዚህ ከእኛ ጋር ይገኛሉ፤ እነርሱ እምቢልታ መንፋት እንደ ጀመሩም እኛ በእናንተ ላይ ጦርነት እንከፍታለን፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከቶ ድል ማድረግ ስለማትችሉ፥ ከቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት አትግጠሙ!”
ሙሴም ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው በካህኑ በአልዓዛር ልጅ በፊንሐስ መሪነት ወደ ጦርነት ላካቸው፤ ፊንሐስም ከመቅደሱ አንዳንድ ንዋየ ቅድሳትንና ለጦርነት መቀስቀሻ (ክተት) የሚሆን መለከት በእጁ ይዞ ነበር።
“ጠላቶችህን ለመውጋት ስትዘምት፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ ከአንተ የሚበልጥም ሠራዊት ባየህ ጊዜ ከግብጽ ምድር ያወጣህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ አትፍራቸው፤
‘የእስራኤል ሰዎች ሆይ! አድምጡ! እነሆ፥ ዛሬ ወደ ጦርነት መሄዳችሁ ነው፤ ከጠላቶቻችሁ የተነሣ አትፍሩ! ወኔአችሁ አይቀዝቅዝ፤ አትሸበሩም!
ዳዊትም ሳኦልን “ንጉሥ ሆይ! ከዚህ ፍልስጥኤማዊ የተነሣ ማንም ሰው መፍራት የለበትም! እኔ ያንተ አሽከር ሄጄ እርሱን እዋጋዋለሁ” አለው።