እነሆ፥ ምድሪቱ በፊታችሁ ናት፤ እኔ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ላወርሳቸው የተስፋ ቃል የገባሁላቸውን ምድር ሄዳችሁ ውረሱ።’ ”
ዘዳግም 2:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ ‘ተመልከት እኔ ንጉሥ ሲሖንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ አሁን ድል በማድረግ ምድሩን ወርሰህ ስፈርበት።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ “እነሆ፤ ሴዎንንና አገሩን ለእናንተ አሳልፌ ልሰጣችሁ ተነሥቻለሁ፤ አሁንም እርሱን አሸንፋችሁ ምድሩን ለመውረስ ተነሡ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታም፦ ‘ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፦ ‘የሐሴቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሴዎንንና ምድሩን በፊትህ በእጅህ አሳልፌ መስጠት እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛ ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር አለኝ። |
እነሆ፥ ምድሪቱ በፊታችሁ ናት፤ እኔ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ላወርሳቸው የተስፋ ቃል የገባሁላቸውን ምድር ሄዳችሁ ውረሱ።’ ”
“በሞአብ በኩልም ካለፍን በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለን፦ ‘አሁን ተነሥታችሁ የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ የሚገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ከነምድሩ ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ፤ እርሱን ወግታችሁ ምድሩን ውረሱ፤
“ነገር ግን ሲሖን ንጉሥ ሴዎን በእርሱ ግዛት ውስጥ አልፈን እንድንሄድ ባለመፍቀዱ፥ አሁን እንዳደረገው አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሊሰጠው ስለ ፈቀደ ትዕቢተኛና እልኸኛ አደረገው።