ዘዳግም 15:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች በቤታችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤ የነጻችሁ ወይም ያልነጻችሁ ብትሆኑም አጋዘንንና ድኲላን እንደምትበሉ ሁላችሁም እነዚህን ትበላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየከተሞችህም ትበላዋለህ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነውም ሆነ ያልሆነው ሰው፣ እንደ ሚዳቋ ወይም እንደ ዋላ ይበላዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየከተሞችህም ትበላዋለህ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ ይበላዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገርህ ውስጥ ትበላዋለህ፤ ንጹሕ ሰው፥ ንጹሕም ያልሆነ፥ ሚዳቋንና ዋሊያን እንደሚበሉ ይበሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገርህ ደጅ ውስጥ ትበላዋለህ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ ሚዳቍና ዋላ እንደሚበሉ ይበሉታል። |