ዘዳግም 11:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተአምራቱንና እርሱ በግብጽ ንጉሥና በመላው አገሩ ላይ ያደረገውን ድንቅ ሥራ ሁሉ አይታችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ መካከል፣ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ መካከል፥ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅም መካከል በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንና በሀገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ድንቅ ሥራዉን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ሥራውን፥ |
እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ የግብጽን ሠራዊት ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው በቀይ ባሕር በማስጠም እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ለዘለቄታው እንደ ደመሰሳቸው አይታችኋል።
ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?
በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን ታላላቅ መቅሠፍቶች፥ ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክህ አንተን ነጻ ያወጣበትን ታላቅ ኀይሉንና ሥልጣኑን አስታውስ፤ ግብጻውያንን ባጠፋበት ዐይነት ዛሬ አንተ የምትፈራቸውን እነዚህንም ሕዝቦች ሁሉ ያጠፋቸዋል።