ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
ዘዳግም 11:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም ዛሬ እኔ የማዛችሁን ሕግ ሁሉ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁንም ውደዱ፤ በፍጹም ልባችሁም አገልግሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፣ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትወድዱና በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል በታማኝነት ብትጠብቁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ |
ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
“‘እንግዲህ የሚያዳምጡኝ ከሆኑ እነዚህ ሕዝብ ትእዛዜን እንዲጠብቁ ንገራቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው በከተማይቱ በሮች አይግቡ፤ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርገው ያክብሩ እንጂ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩ።
“እንግዲህ እስራኤል ሆይ! እግዚአብሔር አምላክህን እንድትፈራው፥ በመንገዱ ሁሉ እንድትሄድ፥ እንድትወደው በሙሉ ልብህና በሙሉ ሐሳብህ እንድታመልከው፥ ለደኅንነትህ ሲባል እኔ ዛሬ የማዝህን የእግዚአብሔር አምላክህን ትእዛዝና ድንጋጌ እንድትጠብቅ ነው እንጂ እርሱ ሌላ ከአንተ ምን ይፈልጋል?
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ብትታዘዝና ዛሬ እኔ የምሰጥህንም ትእዛዞች ሁሉ በታማኝነት ብትጠብቅ፥ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤
“እነዚህን ትእዛዞች ብታዳምጥና በታማኝነትም ብትፈጽማቸው፥ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ በመሐላ የሰጠውን ቃል ኪዳንና ዘለዓለማዊ ፍቅር ለአንተም ያጸናልሃል፤