“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
ዘዳግም 11:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችን ምድር የሚንከባከባትና ዓመቱን ሙሉ የሚጠብቃት እግዚአብሔር አምላክህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች ምድር አምላክህ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፣ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ምን ጊዜም የማይለያት ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህች ምድር ጌታ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፥ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የጌታ የአምላክህ ዐይን ምንጊዜም የማይለያት ናት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት ሀገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእርስዋ ላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር የሚጎበኛት አገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ ነው። |
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
ይህም ሁሉ የሚሆነው ንጉሠ ነገሥቱ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር ወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤ ምድሪቱም የወይራ ፍሬና የወይራ ዘይት እንዲሁም ማር. የሞላባት ናት፤ ንጉሠ ነገሥቱ የሚያዛችሁን ብትፈጽሙ በሕይወት ትኖራላችሁ እንጂ አትሞቱም፤ ስለዚህ ሕዝቅያስ ‘እግዚአብሔር ይታደጋችኋል’ እያለ በመስበክ አያሞኛችሁ፤
ነገር ግን የአይሁድ መሪዎችን እግዚአብሔር ይጠብቃቸው ስለ ነበር ለፋርስ ባለ ሥልጣኖች ለዳርዮስ መልእክት ጽፈው መልስ እስከሚያገኙ ድረስ ሥራውን ከመቀጠል አልከለከሉአቸውም።
ይህም የሚሆነው ንጉሡ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር የወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤