ዘዳግም 1:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ በመከተል ወደ በረሓው ተመልሳችሁ ሂዱ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን፣ ተመልሳችሁ ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ ይዛችሁ ወደ ምድረ በዳው ተጓዙ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር አቅጣጫ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ። |
እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ የግብጽን ሠራዊት ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው በቀይ ባሕር በማስጠም እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ለዘለቄታው እንደ ደመሰሳቸው አይታችኋል።
“እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ምድረ በዳ ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው አቅጣጫ በመጓዝ የኤዶምን ኮረብታማ ቦታ ለብዙ ቀን ዞርን።