ዳንኤል 5:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ስጦታው ለአንተ ይሁን፤ ሽልማቱንም ለሌላ ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን አንብቤ ትርጒሙን እነግርሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ስጦታዎችህን ለራስህ አድርግ፤ ሽልማቶችህንም ለሌላ ሰው ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነብባለሁ፤ ትርጕሙ ምን እንደ ሆነም እነግረዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ዳንኤል መለሰ በንጉሡም ፊት እንዲህ አለ፦ ስጦታህ ለአንተ ይሁን፥ በረከትህንም ለሌላ ስጥ፥ ነገር ግን ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነብባለሁ ፍቺውንም አስታውቃለሁ። |
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን፥ “እኔ አንተን የምረዳህ ስለምንድን ነው? ሄደህ አባትህና እናትህ ይጠይቁአቸው የነበሩትን እነዚያን ነቢያት ጠይቅ!” አለው። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ፥ “አይደለም እኮ! ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞአብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።
ኤልሳዕም “በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ምንም ነገር አልቀበልም” ሲል መለሰለት። ንዕማንም ስጦታውን እንዲቀበልለት አጥብቆ ቢለምነውም ኤልሳዕ ሊቀበለው አልፈቀደም፤
ኤልሳዕም “ሰውየው ሊያነጋግርህ ከሠረገላው ላይ ሲወርድ እኔ በመንፈስ ከአንተ ጋር አልነበርኩምን? እነሆ አሁን ገንዘብና ልብስ፥ የወይራና የወይን ተክል ቦታ፥ በግና የቀንድ ከብት ወይም አገልጋዮችን ለመቀበል ጊዜው አይደለም!
ሕልሙን ከነትርጒሙ ልትነግሩኝ ብትችሉ ግን ሽልማትና ስጦታ ከታላቅ ክብር ጋር እንድታገኙ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ሕልሙን ከነትርጒሙ ንገሩኝ።”
ከዚህም በኋላ ብልጣሶር ወዲያውኑ ዳንኤልን መጐናጸፊያ እንዲያለብሱት፥ የወርቅ ኒሻን በአንገቱ እንዲያደርጉለትና በመንግሥቱም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ እንዲይዝ እንዲያደርጉት በዐዋጅ አዘዘ።