Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 5:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ስጦታዎችህን ለራስህ አድርግ፤ ሽልማቶችህንም ለሌላ ሰው ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነብባለሁ፤ ትርጕሙ ምን እንደ ሆነም እነግረዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ስጦታው ለአንተ ይሁን፤ ሽልማቱንም ለሌላ ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን አንብቤ ትርጒሙን እነግርሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የዚያን ጊዜም ዳንኤል መለሰ በንጉሡም ፊት እንዲህ አለ፦ ስጦታህ ለአንተ ይሁን፥ በረከትህንም ለሌላ ስጥ፥ ነገር ግን ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነብባለሁ ፍቺውንም አስታውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 5:17
8 Referencias Cruzadas  

ነቢዩም፣ “የማገለግለውን ሕያው እግዚአብሔርን፣ ምንም ነገር አልቀበልም” ሲል መለሰ። ምንም እንኳ ንዕማን አስጨንቆ ቢለምነውም አልተቀበለም።


‘አብራምን አበለጸግሁት’ እንዳትል፣ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አንዳች አልፈልግም።


ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለመግዛት አስበሃልና፣ አንተም ገንዘብህም ዐብራችሁ ጥፉ!


ከዚህ በኋላ በቤልሻዛር ትእዛዝ ዳንኤልን ሐምራዊ መጐናጸፊያ አለበሱት፣ የወርቅ ሐብል በዐንገቱ ላይ አጠለቁለት፤ የመንግሥቱም ሦስተኛ ገዥ ሆኖ ተሾመ።


ነገር ግን ሕልሙንና ትርጕሙን ብትነግሩኝ፣ ስጦታና ሽልማት፣ ታላቅ ክብርም ከእኔ ትቀበላላችሁ፤ ሕልሙን ንገሩኝ፤ ትርጕሙንም አሳውቁኝ።”


ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም።


ኤልሳዕ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ሊገናኝህ ከሠረገላው ሲወርድ፣ መንፈሴ ከአንተ ጋራ አልሄደምን? እንዲያው ለመሆኑ ጊዜው ገንዘብና ልብስ፣ የወይራ ዘይት ተክልና የወይን ተክል ቦታ፣ የበግና የከብት መንጋ፣ ወንድና ሴት አገልጋይ የሚቀበሉበት ነውን?


ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፤ “ከአንተ ጋራ ምን የሚያገናኘን ጕዳይ አለና መጣህ፤ አሁን የአባትህና የእናትህ ነቢያት ወዳሉበት ሂድ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፣ “ይህማ አይሆንም፤ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጠን እኛን ሦስት ነገሥታት አንድ ላይ የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios