ዳንኤል 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ ንግሥት የነበረችው የንጉሡ እናት የንጉሡንና የመኳንንቱን ሁካታ ሰምታ ወደ ግብዣው አዳራሽ በመግባት እንዲህ አለች፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር! በዚህ ጉዳይ ይህን ያኽል ልትጨነቅና ፊትህም ሊገረጣ አይገባም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንግሥቲቱም የንጉሡንና የመኳንንቱን ድምፅ ሰምታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገባች፤ እንዲህም አለች፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ አትደንግጥ፤ ፊትህም አይለዋወጥ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግሥቲቱም ስለ ንጉሡና ስለ መኳንንቱ ቃል ወደ ግብዣ ቤት ገባች፥ ንግሥቲቱም ተናገረች እንዲህም አለች፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፥ አሳብህ አያስቸግርህ፥ ፊትህም አይለወጥ። |