Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 13:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ ግን በሐሰት የተሞላችሁ ናችሁ፤ ማንንም መፈወስ እንደማይችሉ ሐኪሞች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁም የማትጠቅሙ ሐኪሞች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁ የማትጠቅሙ ባለ መድኃኒቶች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 13:4
23 Referencias Cruzadas  

እኔም “ይህ የምትለው ነገር ሁሉ ምንም እውነትነት የሌለውና አንተ ራስህ የፈለሰፍከው ሐሰት ነው” ብዬ መለስኩለት።


“ይህን የመሰለ ንግግር ብዙ ጊዜ ሰምቼአለሁ፤ እናንተ አሰልቺ አጽናኞች ናችሁ።


እናንተም እኮ ይህን ሁሉ ታውቃላችሁ፤ ታዲያ ይህን ከንቱ ነገር ለምን ትናገራላችሁ?”


ወንድሞቼ ግን ጐርፉ ከወረደ በኋላ እንደሚደርቁና እንደማያስተማምኑ ወንዞች አታላዮች ናቸው።


የተማመኑበትን ወንዝ ደርቆ ሲያገኙ ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ወደ ቦታውም ሲደርሱ ይበሳጫሉ።


እናንተም ለእኔ እንደ እነዚያ ደረቅ ወንዞች ናቸሁ። የደረሰብኝን መከራ አይታችሁ ወደ ኋላ አፈገፈጋችሁ።


ምንም እንኳ ትዕቢተኞች በሐሰት ስሜን ቢያጠፉ እኔ ትእዛዞችህን በሙሉ ልቤ እጠብቃለሁ።


“በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር፤


እነሆ እኔ እግዚአብሔር የምለውን አድምጡ! በሐሰት የተሞላ ሕልማቸውን የሚናገሩ ነቢያትን እጠላለሁ፤ ይህን ሕልም እየተናገሩ ሐሰት በተሞላ ትምክሕታቸው ሕዝቤን ከእውነተኛ መንገድ ያወጣሉ፤ እኔ አላክኋቸውም፤ ወይም ሂዱልኝ አላልኳቸውም፤ ለሕዝቡም የሚሰጡት ጥቅም የለም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ለእናንተ የሚከራከርላችሁ የለም፤ ለቊስላችሁም መድኃኒት አይገኝም፤ እናንተም አትድኑም።


እንደ ድንግል የምትታዪ ግብጽ ሆይ! ወደ ገለዓድ ሄደሽ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጊ፤ የአንቺ መድኃኒት ሁሉ ከንቱ ነው፤ ሊፈውስሽ የሚችል ነገር ከቶ የለም።


የሕዝቤንም የስብራት ቊስል እንደ ቡጭራት በመቊጠር በሚገባ አያክሙትም፤ እንዲሁም ሰላም ሳይኖር ‘ሰላም ነው፤ ሰላም ነው፤’ ይላሉ።


በገለዓድ የቅባት መድኃኒት የለምን? ሐኪሞችስ በዚያ አይገኙምን? ታዲያ ሕዝቤ የማይፈወሱት ስለምንድን ነው?


የደከሙትን አላበረታቸሁም፤ የታመሙትን አላዳናችሁም፤ የተሰበሩትን አልጠገናችሁም፤ የባዘኑትን አልመለሳችሁም፤ የጠፉትን አልፈለጋችሁም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በግፍና በጭካኔ ገዛችኋቸው።


“እስራኤል መታመሙን፥ ይሁዳም መቊሰሉን ባየ ጊዜ፥ እስራኤል ወደ አሦር ፊቱን መለሰ፤ ርዳታም ለማግኘት ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ ነገር ግን እርሱ ሊያድናቸው ወይም ቊስላቸውን ሊፈውስ አልቻለም።


ኢየሱስም ይህን ሰምቶ፦ “በሽተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤ እኔም የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት ነው፤” አላቸው።


ከሐኪም ወደ ሐኪም በመሄድ ብዙ ተሠቃይታና ገንዘብዋንም ሁሉ ጨርሳ ነበር። ነገር ግን እየባሰባት ሄደ እንጂ ምንም አልተሻላትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos