ዳንኤል 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አሁንም ብልጣሶር ሆይ፤ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሁሉ አንዳቸውም ሊተረጕሙልኝ ስላልቻሉ፣ ምን ማለት እንደ ሆነ ንገረኝ። አንተ የአማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጕምልኝ ትችላለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ፥ አንተም፥ ብልጣሶር፥ ፍቺውን አስታውቀኝ፥ የመንግሥቴ ጠቢባን ሁሉ ፍቺውን ያስታውቁኝ ዘንድ አይችሉምና፥ ነገር ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ አለና አንተ ትችላለህ። |
ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።
ግብጻውያን ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ዕቅዳቸውም ተግባራዊ እንዳይሆን አደርጋለሁ፤ በዚህም ጊዜ እንዲረዱአቸው ጣዖቶቻቸውን ይጠይቃሉ፤ ሙታንን ወደሚጠሩ ጠንቋዮቻቸው ሄደው ይማከራሉ፤ ከሙታን መናፍስትም ምክር ይጠይቃሉ።
ጥበብና ማስተዋልን በተመለከቱ ጉዳዮች ንጉሡ በሚጠይቃቸው ነገሮች በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ከሚገኙ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ብልጫ ያላቸው ሆነው አገኛቸው።
እነሆ፥ ጠቢባን አማካሪዎቼና አስማተኞች ሁሉ ይህን ጽሕፈት አንብበው እንዲተረጒሙልኝ ተጠርተው ወደ እኔ መጥተው ነበር፤ ነገር ግን ተርጒመው ሊያስረዱኝ አልቻሉም፤
ጥበበኞቹም ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ነገር ግን ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጒሙን ለንጉሡ ማስረዳት የቻለ ከእነርሱ መካከል የተገኘ ማንም አልነበረም።