ዳንኤል 4:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 “እኔ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አሁንም ብልጣሶር ሆይ፤ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሁሉ አንዳቸውም ሊተረጕሙልኝ ስላልቻሉ፣ ምን ማለት እንደ ሆነ ንገረኝ። አንተ የአማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጕምልኝ ትችላለህ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 “እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ፥ አንተም፥ ብልጣሶር፥ ፍቺውን አስታውቀኝ፥ የመንግሥቴ ጠቢባን ሁሉ ፍቺውን ያስታውቁኝ ዘንድ አይችሉምና፥ ነገር ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ አለና አንተ ትችላለህ። Ver Capítulo |