ዳንኤል 3:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስቱ ሰዎች ግን በጥብቅ እንደ ታሰሩ በእሳቱ ነበልባል ላይ ወደቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ግን ተጠፍረው እንደ ታሰሩ በሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብድናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ። |
በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።
ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።
ከዚያን በኋላ ንጉሡ ናቡከደነፆር በመደነቅ ፈጥኖ ተነሣና “አስረን በሚነደው የእሳት ነበልባል ውስጥ የጣልናቸው ሰዎች ሦስት ብቻ አልነበሩምን?” ሲል አማካሪዎቹን ጠየቀ። እነርሱም “አዎ፥ ንጉሥ ሆይ!” አሉት።
የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከደካማነት ወደ ብርቱነት ተለወጡ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የወራሪ ጠላትን ወታደሮች አባረሩ፤