ዳንኤል 2:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራውን ዳንኤልን “ያየሁትን ሕልም ከነትርጒሙ ልትነግረኝ ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ብልጣሶር የተባለውን ዳንኤልን፣ “ያየሁትን ሕልምና ትርጕሙን ልትነግረኝ ትችላለህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም መለሰ ብልጣሶርም የሚባለውን ዳንኤልን፦ ያየሁትን ሕልምና ፍቺውን ታስታውቀኝ ዘንድ ትችላለህን? አለው። |
ከዚህ በኋላ በአምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራው ዳንኤል ገባ፤ ይህ ሰው የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያደረበት ነው፤ እንዲህም ስል ሕልሜን ነገርኩት፤
እርሱ ሕልምን በመተርጐም፥ እንቆቅልሽን በመፍታትና የተሰወረውን ምሥጢር ገልጦ በማስረዳት ልዩ ችሎታ ያለው ጥበበኛና ብልኅ ሰው ነው፤ ስለዚህ ያንን አባትህ ናቡከደነፆር ‘ብልጣሶር’ ብሎ የሠየመውን ዳንኤልን አስጠራ፤ እርሱ ይህን ሁሉ ነገር ተርጒሞ ያስረዳሃል።”
አንተ ግን የተሰወረውን ነገር የመተርጐምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ሁሉ የመፍታት ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ይህን ጽሕፈት አንብበህ ትርጒሙን ብትነግረኝ፥ ሐምራዊ መጐናጸፊያ እንድትለብስ፤ የወርቅ ኒሻን በአንገትህ እንድታደርግና በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ እንድትይዝ አደርጋለሁ።”
የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፤ ዳንኤል ሕልምና ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ያየውን ሕልም ጻፈ።
ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።