Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ በአምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራው ዳንኤል ገባ፤ ይህ ሰው የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያደረበት ነው፤ እንዲህም ስል ሕልሜን ነገርኩት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በመጨረሻም በአምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል ገብቶ በፊቴ ቆመ፤ ሕልሜንም ነገርሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በመጨረሻም የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር የሚባለው ዳንኤል በፊቴ ገባ፥ እኔም ሕልሙን ነገርሁት እንዲህም አልሁት፦

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 4:8
14 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም “የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ከዮሴፍ የተሻለ ሰው ከቶ አናገኝም” አላቸው።


“ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው።


ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የነበረበትን የቀድሞውን ዘመን ማስታወስ ጀመሩ፤ ከመንጋዎቹ እረኞች ጋር ከባሕር ያወጣቸው እግዚአብሔር የት አለ? ቅዱስ መንፈሱን በውስጣቸው ያሳደረው እግዚአብሔር የት ነው?


“ለአሕዛብ ሁሉ በማወጅ ወሬውን ንገሩ! አርማ አንሥታችሁ ዜናውን አስታውቁ! ከቶ ምሥጢር አድርጋችሁ አታስቀሩ! እነሆ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል የተባለው ጣዖት እንዲያፍር ተደረገ፤ ‘ማርዱክ’ የተባለ ጣዖቷም ተሰባብሮአል፤ የባቢሎን ጣዖቶች አፍረዋል፤ አጸያፊ ምስሎችዋም ተሰባብረዋል።


የምተክለው በእስራኤል በሚገኝ በከፍተኛ ተራራ ላይ ነው፤ ይህንንም የማደርገው ቅርንጫፎችን አስገኝቶ ፍሬ በማፍራት የተዋበ የሊባኖስ ዛፍ እንዲሆን ነው። በሥሩም የተለያዩ ወፎች ይኖሩበታል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ክንፍ ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ ጎጆዎቻቸውን ይሠሩበታል።


የንጉሡም ባለሟሎች አለቃ ስማቸውን በመለወጥ ዳንኤልን ብልጣሶር፤ ሐናንያን ሲድራቅ፤ ሚሳኤልን ሚሳቅ፤ ዐዛርያን አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።


ንጉሥ ሆይ! አንተ ለምታቀርበው ከባድ ጥያቄ ከአማልክት በቀር መልስ መስጠት የሚችል የለም፤ አማልክት ደግሞ በሰው መካከል የሚኖሩ አይደሉም።”


ንጉሡም ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራውን ዳንኤልን “ያየሁትን ሕልም ከነትርጒሙ ልትነግረኝ ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው።


ናቡከደነፆርም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ! አማልክቴን አለማምለካችሁና ላቆምኩትም የወርቅ ምስል አለመስገዳችሁ እርግጥ ነውን?


“እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።”


‘የጠቢባን አለቃ የሆንክ ብልጣሶር ሆይ፥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ምሥጢር ሁሉ ለአንተ ሰውር እንደማይሆን ዐውቃለሁ፤ እነሆ፥ ያየሁትን ሕልም ልንገርህና ተርጒምልኝ።’


የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ እንዳለና ብልኀት፥ ዕውቀትና ጥበብ የተሰጠህ መሆኑን ሰምቼአለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos