ዳንኤል 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የደቡብ ንጉሥ ማለትም የግብጽ ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከእርሱ ይልቅ የበረታ ሆኖ እጅግ ታላቅ ለሆነ መንግሥት መሪ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የደቡቡ ንጉሥ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፤ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደቡብም ንጉሥ ከአለቆቹም አንዱ ይበረታሉ፥ እርሱም ይበረታበታል ይሠለጥንማል፥ ግዛቱም ታላቅ ግዛት ይሆናል። |
ከዚያ በኋላ ብዙ ሰዎች በግብጽ ንጉሥ ላይ ያምፃሉ፤ ዳንኤል ሆይ! በዚህ ራእይ የታየው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ከአንተም ወገኖች አንዳንድ የዐመፅ ሰዎች ሁከት ያስነሣሉ፤ ነገር ግን አይሳካላቸውም።
“ትልቅ የጦር ኀይል አደራጅቶ በድፍረት በግብጽ ንጉሥ ላይ ይዘምታል፤ የግብጽ ንጉሥም በበኩሉ እጅግ ታላቅ የሆነ የጦር ኀይል አዘጋጅቶ የመጣበትን ጦር ይመክታል፤ ነገር ግን የግብጹ ንጉሥ ሤራ ስለሚደረግበት አይሳካለትም።
“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።
በጥቋቊር ፈረሶች ይሳብ የነበረው ሠረገላ ወደ ሰሜን፥ በነጫጭ ፈረሶች ይሳብ የነበረው ወደ ምዕራብ፥ በቡራቡሬ ፈረሶች ይሳብ የነበረው ወደ ደቡብ አገሮች ይሄዱ ነበር።