ዳንኤል 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብና ማስተዋልን በተመለከቱ ጉዳዮች ንጉሡ በሚጠይቃቸው ነገሮች በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ከሚገኙ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ብልጫ ያላቸው ሆነው አገኛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ በጠየቃቸው በማንኛውም የጥበብና የማስተዋል ጕዳይ በመላ ግዛቱ ካሉት አስማተኞችና ድግምተኞች ሁሉ ዐሥር እጅ በልጠው አገኛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም በጠየቃቸው በጥበብና በማስተዋል ነገር ሁሉ በግዛቱ ሁሉ ከሚኖሩ የሕልም ተርጓሚዎችና አስማተኞች ሁሉ እነርሱ አሥር እጅ የበለጡ ሆነው አገኘባቸው። |
ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።
ከዚህ በኋላ የንጉሡ አስማተኞች በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ፤ ንጉሡም ልቡን በማደንደን ጸና፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ማዳመጥ እምቢ አለ።
አስማተኞቹም “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!” ብለው ለንጉሡ ነገሩት፤ ንጉሡ ግን ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።
ግብጻውያን ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ዕቅዳቸውም ተግባራዊ እንዳይሆን አደርጋለሁ፤ በዚህም ጊዜ እንዲረዱአቸው ጣዖቶቻቸውን ይጠይቃሉ፤ ሙታንን ወደሚጠሩ ጠንቋዮቻቸው ሄደው ይማከራሉ፤ ከሙታን መናፍስትም ምክር ይጠይቃሉ።
እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።
እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው።
ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ስጦታው ለአንተ ይሁን፤ ሽልማቱንም ለሌላ ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን አንብቤ ትርጒሙን እነግርሃለሁ።
ከእነዚህ ሕዝብ አንዱም ወደዚያች ምድር ለመግባት በሕይወት አይኖርም፤ በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግኋቸውን ተአምራት ሁሉ አይተዋል፤ ነገር ግን የትዕግሥቴን ብዛት ደጋግመው በመፈታተን ለእኔ መታዘዝ እምቢ አሉ።