አሞጽ 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፦ “እናንተ በመንጠቆ ተይዞ እንደሚወሰድ ነገር የምትወሰዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ከእናንተ እስከ መጨረሻ የቈዩት እንኳ በመንጠቆ ተይዘው እንደሚወሰዱ ዐሣዎች ይወሰዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሏል፤ “እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት ትሩፋናችሁ እንኳ፣ በዓሣ መንጠቆ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሜንጦ፥ ትሩፋቶቻችሁንም በመንጠቆ የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ አግዚአብሔር፥ “እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን እነሆ በላያችሁ ይመጣል” ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል። |
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ሕዝብ እንደ ዓሣ የሚያጠምዱና እንደ አውሬ የሚያድኑ ብዙ ሰዎችን እልካለሁ፤ በየተራራውና በየኰረብታው በቋጥኞች ውስጥ ባሉ ዋሻዎችም እያደኑ ይይዙአቸዋል።
በመንጋጋህ መቃጥን አስገባለሁ፤ በወንዝህ ውስጥ ያሉትንም ዓሣዎች በሰውነትህ ላይ እንዲጣበቁ አደርጋለሁ፤ ዓሣዎቹም በአንተ ላይ እንደ ተጣበቁ ከዓባይ ወንዝ ጐትቼ አወጣሃለሁ።
“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።
በመንጋጋው መንጠቆ አስገብቼ በመጐተት እርሱንና ሠራዊቱን ወደ መጡበት ወደ ኋላቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ሠራዊቱ ከፈረሶችና የጦር ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞቹ ጋር እጅግ የበዛ ነው፤ እያንዳንዱ ወታደር ትልቅና ትንሽ ጋሻ አንግቦ ሰይፍ ታጥቆአል፤
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።