35 “በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ በቅዱስ ስሜ ስለ ማልኩ ለዳዊት ከቶ አልዋሽም።
35 አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣ ዳዊትን አልዋሸውም።
35 ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም።
እግዚአብሔር “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ትሆናለህ” ብሎ ማለ፤ መሐላውም የማይሻር ነው።
እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲህ ሲል የማይሻር ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከልጆችህ አንዱን አነግሠዋለሁ፤
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፦ “እናንተ በመንጠቆ ተይዞ እንደሚወሰድ ነገር የምትወሰዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ከእናንተ እስከ መጨረሻ የቈዩት እንኳ በመንጠቆ ተይዘው እንደሚወሰዱ ዐሣዎች ይወሰዳሉ።
ለያዕቆብና ለዘሮቹ መመኪያ የሆነው እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፦ “እነርሱ የሠሩትን ሥራ ሁሉ አልረሳም።
እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።
ይህም እምነት በዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የማይዋሸው አምላክ ይህን ሕይወት ለመስጠት ከዘመናት በፊት ቃል ገባልን።
እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ የሚምልበት ከእርሱ የበለጠ ሌላ ማንም ስለሌለ እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፤
በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ውሳኔው የማይለወጥ መሆኑን ለማስረዳት ፈልጎ ለተስፋው ወራሾች ተስፋውን በመሐላ አጸናላቸው።