La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 28:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎቹም “ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል፤ ወይም በድንገት ሞቶ ይወድቃል” በማለት ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም ጒዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ አሳባቸውን ለወጡና “ይህስ አምላክ ነው!” አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ሞቶ ይወድቃል ብለው ይጠባበቁ ነበር፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ጠብቀው ምንም የተለየ ነገር እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ፣ ሐሳባቸውን ለውጠው፣ “ይህስ አምላክ ነው” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም “ሊያብጥ ወይም ወዲያው ሞቶ ሊወድቅ ነው፤” ብለው ይጠባበቁት ነበር ብዙ ጊዜ ግን ሲጠባበቁ በእርሱ ላይ የሚያስገርም ነገር ምንም ባላዩ ጊዜ “ይህስ አምላክ ነው፤” ብለው አሳባቸውን ለወጡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ርሱ ግን ወዲ​ያ​ውኑ የሚ​ያ​ብጥ ወይም ሞቶ የሚ​ወ​ድቅ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር። እያ​ዩ​ትም ብዙ ሰዓት ቆሙ፤ አን​ዳ​ችም እንደ አል​ጐ​ዳው በአዩ ጊዜም፥ “ይህስ አም​ላክ ነው” ብለው ቃላ​ቸ​ውን ለወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም፦ “ሊያብጥ ወይም ወዲያው ሞቶ ሊወድቅ ነው” ብለው ይጠባበቁት ነበር ብዙ ጊዜ ግን ሲጠባበቁ በእርሱ ላይ የሚያስገርም ነገር ምንም ባላዩ ጊዜ፦ “ይህስ አምላክ ነው” ብለው አሳባቸውን ለወጡ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 28:6
6 Referencias Cruzadas  

ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


ጲላጦስም “ታዲያ፥ መሲሕ የተባለውን ኢየሱስን ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም “ይሰቀል!” ሲሉ መለሱ።


ሕዝቡም “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው ድምፅ አይደለም!” እያሉ ጮኹ።


በዚያ በነበርንበት ስፍራ አጠገብ የደሴቲቱ ገዢ የፑፕልዮስ መሬት ነበር፤ ይህ ሰው በቤቱ ተቀብሎን ሦስት ቀን በጥሩ ሁኔታ አስተናገደን።


ሰዎች ሁሉ ትንሹም ትልቁም “ይህ ሰው ታላቅ ተብሎ የሚጠራው የእግዚአብሔር ኀይል ነው!” እያሉ በጥንቃቄ ያዳምጡት ነበር።