በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 28:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሮም በገባን ጊዜ ጳውሎስ አንድ የሚጠብቀው ወታደር ተሰጠውና ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮም በደረስን ጊዜም፣ ጳውሎስ ይጠብቀው ከነበረው ወታደር ጋራ ለብቻው በዚያ እንዲቈይ ተፈቀደለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ተፈቀደለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ የመቶ አለቃው እስረኞችን ለሠራዊቱ አለቃ አስረከበ፤ ጳውሎስ ግን ከሚጠብቀው አንድ ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ፈቀደለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ተፈቀደለት። |
በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።
ናቡከደነፆር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፥ አምስተኛው ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ናቡዛርዳን ተብሎ የሚጠራው የናቡከደነፆር የክብሩ ዘበኞቹ አዛዥ ኢየሩሳሌም ገባ።
የክብር ዘብ አዛዡ እኔን ገለል አድርጎ ለብቻ እንዲህ አለኝ፦ “አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን ምድር እንደሚያጠፋት አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤
እዚያ የጳንጦስ ተወላጅ የሆነውን አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኘ፤ የሮም ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ አዞ ስለ ነበረ አቂላ ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ ገና መምጣቱ ነበር፤ ስለዚህ ጳውሎስ ወደ እነርሱ ሄዶ ተዋወቃቸው፤
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
በፍርግያ፥ በጵንፍልያ፥ በግብጽ፥ በቀሬና አጠገብ ባሉት በሊቢያ አውራጃዎች የምንኖር ነን፤ ከሮምም የመጣን አይሁድና ወደ አይሁድነትም የገባን እንገኛለን፤
ጳውሎስን ይጠብቅ የነበረውንም መቶ አለቃ “እምብዛም ነጻነት ሳትከለክለው በጥንቃቄ ጠብቀው፤ ወዳጆቹም የሚያስፈልገውን ሁሉ ይዘውለት ሲመጡ አትከልክልበት” አለው።
የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ስለ ፈለገ አሳባቸውን አልተቀበለም፤ ይልቁንም መዋኘት የሚችሉ አስቀድመው ከመርከቡ ወደ ባሕር እየዘለሉ ወደ ምድር እንዲወጡ አዘዘ።