ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ።
ሐዋርያት ሥራ 27:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልሕቆቹን ፈተው በባሕር ውስጥ ለቀቁአቸው፤ በዚያኑ ጊዜም የመቅዘፊያውን ገመዶች ፈቱ፤ ከዚህ በኩል ያለውን ሸራ ወደ ነፋሱ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፤ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልሕቁንም ፈትተው በባሕር ላይ ጣሉት፤ የሚያቆሙበትንም አመቻችተው እንደ ነፋሱ አነፋፈስ መጠን ትንሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳርቻም ሄድን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፥ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። |
ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ።
ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፥ ዓሣ አጥማጆች የነበሩትን ሁለት ወንድማማች እነርሱም ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን፥ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ።
መርከበኞቹ ጀልባውን ወደ መርከቡ ስበው ካወጡት በኋላ በመርከቡ ዙሪያ ገመድ ጠመጠሙ፤ መርከቡ ሱርቲስ ወደምትባል አሸዋማ ስፍራ እንዳይወድቅ ፈርተው ሸራውን አወረዱና በነፋስ እየተነዱ ሄዱ።
ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቊልል ጋር በመጋጨቱ ቊልቊል ተደፋ፤ በስተፊቱም ወደ ታች ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊት የተነሣ ይሰባበር ጀመር።