Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 27:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 መርከበኞቹ ጀልባውን ወደ መርከቡ ስበው ካወጡት በኋላ በመርከቡ ዙሪያ ገመድ ጠመጠሙ፤ መርከቡ ሱርቲስ ወደምትባል አሸዋማ ስፍራ እንዳይወድቅ ፈርተው ሸራውን አወረዱና በነፋስ እየተነዱ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጀልባዋንም ወደ ላይ ጐትተው ካወጧት በኋላ መርከቧ እንዳትፈራርስ ዙሪያዋን በገመድ ጠምጥመው አሰሯት፤ ስርቲስ ከተባለው አሸዋማ ደለል ጋራ ሄደው እንዳይላተሙ ስለ ፈሩም፣ የመርከቧን ሸራ አውርደው እንዲሁ በዘፈቀደ እንድትነዳ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወደ ላይም ካወጡአት በኋላ መርከቡን በገመድ አስታጥቀው አጸኑ፤ ስርቲስም ወደሚሉት ወደ አሸዋ እንዳይወድቁ ፈርተው ሸራውን አውርደው እንዲሁ ተነዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከዚህ በኋላ ተጋ​ግ​ዘን በገ​መድ አጠ​ና​ከ​ር​ናት፤ ከዚ​ህም ቀጥሎ ቀዛ​ፊ​ዎች ወደ ጥልቁ ባሕር እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ በፈሩ ጊዜ ሸራ​ውን አወ​ረዱ፤እን​ዲ​ሁም እን​ድ​ን​ሄድ አደ​ረ​ግን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ ላይም ካወጡአት በኋላ መርከቡን በገመድ አስታጥቀው አጸኑ፤ ስርቲስም ወደሚሉት ወደ አሸዋ እንዳይወድቁ ፈርተው ሸራውን አውርደው እንዲሁ ተነዱ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 27:17
5 Referencias Cruzadas  

መርከባችን በባሕሩ ዳር ካሉ ድንጋዮች እንዳይጋጭ ፈርተው ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቆችን ወደ ባሕሩ አወረዱ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ አልፎ ቀን እንዲመጣላቸው ይጸልዩ ጀመር።


ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቊልል ጋር በመጋጨቱ ቊልቊል ተደፋ፤ በስተፊቱም ወደ ታች ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊት የተነሣ ይሰባበር ጀመር።


ሆኖም ነፋሱ ወደ አንዲት ደሴት ዳርቻ ወስዶ ይጥለናል።”


ቄዳ የተባለችውን ደሴት ተገን አድርገን ስንጓዝ በታላቅ ችግር የመርከቡን ጀልባ ይዘን በቊጥጥራችን ሥር ለማድረግ ቻልን።


መልሕቆቹን ፈተው በባሕር ውስጥ ለቀቁአቸው፤ በዚያኑ ጊዜም የመቅዘፊያውን ገመዶች ፈቱ፤ ከዚህ በኩል ያለውን ሸራ ወደ ነፋሱ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios