በዚያን ጊዜ ጀልባዋ በባሕሩ መካከል ሆና ከምትሄድበት አቅጣጫ በተቃራኒ በሚነፍሰው ነፋስ እየተመታች ማዕበሉ ወዲያና ወዲህ ያንገላታት ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 27:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተነሥተን ነፋሱ ከፊት ለፊት ይነፍስብን ስለ ነበር የቆጵሮስን ደሴት ተገን አድርገን በመርከብ ጒዞአችንን ቀጠልን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ተነሥተን በባሕር ተጓዝን፤ ነፋስ ከፊት ለፊት ስለ ገጠመን፣ የቆጵሮስን ደሴት ተገን አድርገን ዐለፍን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ተነሥተን ነፋሱ ፊት ለፊት ነበረና በቆጵሮስ ተተግነን ሄድን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወጥተን ነፋስ ፊት ለፊት ነበርና በቆጵሮስ በኩል ዐለፍን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ተነሥተን ነፋሱ ፊት ለፊት ነበረና በቆጵሮስ ተተግነን ሄድን፤ |
በዚያን ጊዜ ጀልባዋ በባሕሩ መካከል ሆና ከምትሄድበት አቅጣጫ በተቃራኒ በሚነፍሰው ነፋስ እየተመታች ማዕበሉ ወዲያና ወዲህ ያንገላታት ነበር።
ደቀ መዛሙርቱ ከወደፊታቸው በሚነፍሰው ነፋስ ምክንያት መቅዘፍ ተቸግረው ሲጨነቁ አያቸው፤ ከሌሊቱም ከዘጠኝ እስከ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ አልፎአቸውም ሊሄድ ነበር።
በዚህ ምክንያት በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ከፍ ያለ ክርክር ተነሣና ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ።
በቂሳርያ የነበሩ አንዳንድ ምእመናን አብረውን መጡ፤ እነርሱም በምናሶን ቤት እንድናርፍ ወደ እርሱ ቤት መሩን፤ ይህ ሰው ቀደም ብሎ ያመነ፥ የቆጵሮስ ተወላጅ ነበር።
ብዙ ቀን ቀስ እያልን ተጒዘን በብዙ ችግር ወደ ቀኒዶስ ከተማ አጠገብ ደረስን፤ ነፋሱም ወደፊት እንዳንሄድ ስለ ከለከለን በሰልሞና ርእሰ ምድር ጫፍ አጠገብ አለፍንና የቀርጤስን ደሴት ተገን አድርገን ሄድን።
የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው።