ሐዋርያት ሥራ 21:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በቂሳርያ የነበሩ አንዳንድ ምእመናን አብረውን መጡ፤ እነርሱም በምናሶን ቤት እንድናርፍ ወደ እርሱ ቤት መሩን፤ ይህ ሰው ቀደም ብሎ ያመነ፥ የቆጵሮስ ተወላጅ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በቂሳርያ ከነበሩት ደቀ መዛሙርትም አንዳንዶቹ ወደ ምናሶን ቤት ይዘውን መጡ፤ እኛም በዚያው ተቀመጥን። ምናሶን የቆጵሮስ ሰው ሲሆን፣ ከመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበረ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በቂሣርያም ከነበሩ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶች ደግሞ ከእኛ ጋር መጡ፤ እነርሱም ወደምናድርበት ወደ ቀደመው ደቀመዝሙር ወደ ቆጵሮሱ ምናሶን ወደሚሉት ቤት መሩን። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ከደቀ መዛሙርትም ከቂሳርያ አብረውን የመጡ ነበሩ፤ ሄደንም ከመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ወገን ከሆነው በቆጵሮስ በሚኖረው በምናሶን ቤት አደርን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 በቂሣርያም ከነበሩ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶች ደግሞ ከእኛ ጋር መጡ፥ እነርሱም ወደምናድርበት ወደ ቀደመው ደቀ መዝሙር ወደ ቆጵሮሱ ምናሶን ወደሚሉት ቤት መሩን። Ver Capítulo |