ሐዋርያት ሥራ 27:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ጳውሎስ መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን “እነዚህ መርከበኞች በመርከቡ ላይ ዐርፈው ካልተቀመጡ እናንተ ለመዳን አትችሉም” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም የመቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች መርከቡ ላይ ካልቈዩ እናንተም ልትተርፉ አትችሉም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮች “እነዚህ በመርከቡ ካልቆዩ እናንተ ትድኑ ዘንድ አትችሉም፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጳውሎስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮቹ፥ “እነዚህ ቀዛፊዎች በመርከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አትችሉም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮቹ፦ “እነዚህ በመርከቡ ካልቆዩ እናንተ ትድኑ ዘንድ አትችሉም” አላቸው። |
መርከበኞቹ ከመርከቡ ወጥተው ለመሸሽ ፈልገው ስለ ነበር በመርከቡ በስተፊት መልሕቆችን የሚጥሉ መስለው በመርከቡ ላይ የነበረችውን ጀልባ ወደ ባሕሩ ጣሉ።