ሐዋርያት ሥራ 27:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መርከቡም ስለ ተገፋና ነፋሱን መቋቋም ስላልቻለ ዝም ብለን በነፋሱ እየተነዳን ሄድን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መርከቢቱም በማዕበሉ ስለ ተያዘች፣ ወደ ነፋሱ መግፋት አልቻለችም፤ ስለዚህ መንገድ ለቅቀን በነፋሱ ተነዳን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መርከቡም ተነጥቆ ነፋሱን ሲቃወም መሄድ ስላልቻለ ለቀነው ተነዳን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መርከባችንም ተመትታ ተነጠቀች፤ ቀዛፊዎችም በነፋሱ ፊት ለፊት መቆም አልተቻላቸውምና ተዉአት፤ ብቻዋንም ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መርከቡም ተነጥቆ ነፋሱን ሲቃወም መሄድ ስላልቻለ ለቀነው ተነዳን። |
በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር መካከል ላይ በነፋስ እየተንገላታን ስንሄድ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞች ወደ ምድር የቀረቡ መሰላቸው።