ሐዋርያት ሥራ 25:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊስጦስ ወደ ግዛቱ ወደ ቂሣርያ ገብቶ ሦስት ቀን ከቈየ በኋላ ከዚያ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊስጦስም ወደ አውራጃው ከገባ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ከቂሳርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊስጦስም ወደ አውራጃው ገብቶ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊስጦስም ወደ ቂሣርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነበተ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊስጦስም ወደ አውራጃው ገብቶ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። |
ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከዐሥር ቀኖች ያልበለጠ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠና ጳውሎስን እንዲያቀርቡት አዘዘ።