Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 25:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከጥቂት ቀን በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን “እንኳን ደኅና መጣህ” ለማለት ወደ ቂሳርያ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከጥቂት ቀንም በኋላ፣ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን እጅ ሊነሡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ንጉሡ አግሪጳ በርኒቄም ለፊስጦስ ሰላምታ እንዲያቀርቡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ንጉሡ አግሪጳ በርኒቄም ለፊስጦስ ሰላምታ እንዲያቀርቡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 25:13
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ድል በመንሣቱ ሰላምታና የደስታ መግለጫ ያቀርብለት ዘንድ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቀደም ሲልም ቶዒ በሀዳድዔዜር ላይ ጦርነት ሲያካሄድ የነበረ ነው፤ ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ለዳዊት ይዞለት ሄደ።


ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት።


“የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ በማፌዝ እጅ ይነሡት ነበር።


ፊስጦስ ወደ ግዛቱ ወደ ቂሣርያ ገብቶ ሦስት ቀን ከቈየ በኋላ ከዚያ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።


በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተነጋገረና “ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ካልክ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ትሄዳለህ” አለው።


ፊስጦስ ግን “ጳውሎስ በቂሳርያ በእስር ቤት እየተጠበቀ ነው፤ እኔም አሁን በቶሎ ተመልሼ ወደዚያ እሄዳለሁ፤


አግሪጳ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው፤ ጳውሎስም እጁን ዘረጋና እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ።


ፊልጶስ ግን በአዞጦስ ተገኘ፤ ወደ ቂሳርያም እስከ መጣ ድረስ በየከተሞቹ ሁሉ እየሄደ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።


ይህንንም መሥዋዕት የማቅረቡን ሥርዓት እንደ ፈጸመ ወዲያውኑ ሳሙኤል ደረሰ፤ ሳኦልም ወጥቶ አቀባበል አደረገለት፤


ከናባል አገልጋዮች አንዱም የናባልን ሚስት አቢጌልን እንዲህ አላት፤ “ዳዊት ካለበት በረሓ መልእክተኞችን ከሰላምታ ጋር ወደ ጌታችን ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን በስድብ አዋረዳቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos