ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
ሐዋርያት ሥራ 24:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በሸንጎው ፊት በቀረብኩ ጊዜ ያደረግኹት በደል እንዳለ እነዚህ የቀረቡ ሰዎች ይናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም በዚህ ያሉት እነዚህ በሸንጎው ፊት ቀርቤ በነበረበት ጊዜ ያገኙብኝ ወንጀል ካለ ይናገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም በመካከላቸው ቆሜ ‘ዛሬ ስለ ሙታን መነሣት በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኛል፤’ ብዬ ከጮኽሁት ከዚህ ከአንድ ነገር በቀር፥ በሸንጎ ፊት ቆሜ ሳለሁ በእኔ አንድ ዐመፃ ያገኙ እንደሆን እነዚህ ራሳቸው ይናገሩ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም እኔ በሸንጎ ቆሜ ሳለሁ ያገኙብኝ በደል እንደ አለ እነዚህ ራሳቸው ይመስክሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም በመካከላቸው ቆሜ፦ ዛሬ ስለ ሙታን መነሣት በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኛል ብዬ ከጮኽሁት ከዚህ ከአንድ ነገር በቀር፥ በሸንጎ ፊት ቆሜ ሳለሁ በእኔ አንድ ዓመፃ ያገኙ እንደ ሆን እነዚህ ራሳቸው ይናገሩ። |
ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
ሳሙኤልም “እንግዲህ ዛሬ በፊታችሁ ንጹሕ ሆኜ ስለ መገኘቴ እግዚአብሔርና እርሱ የመረጠው ንጉሥ ምስክሮች ናቸው” አለ። ሕዝቡም “አዎ! እግዚአብሔር ምስክር ነው!” ሲሉ መለሱለት።