ሐዋርያት ሥራ 24:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም ከሄድኩ ከዐሥራ ሁለት ቀን እንደማይበልጥ አንተ ራስህ ማረጋገጥ ትችላለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣሁት ከዐሥራ ሁለት ቀን በፊት መሆኑን አንተው ራስህ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከዐሥራ ሁለት ቀን እንዳይበልጥ ልታውቀው ትችላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ዐሥራ ሁለት ቀን እንደማይሆን ልታውቀው ትችላለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከአሥራ ሁለት ቀን እንዳይበልጥ ልታውቀው ትችላለህ። |
በማግስቱ አዛዡ፥ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበት ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ፈለገ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና የሸንጎው አባሎች በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም ከእስራቱ ፈቶ ወሰደና በፊታቸው አቀረበው።
ከዚህ በኋላ የጦር አዛዡ ከመቶ አለቆቹ ሁለቱን ጠርቶ “ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ወደ ቂሳርያ የሚሄዱ ሁለት መቶ ወታደሮችና ሰባ ፈረሰኞች፤ ሁለት መቶ ጦር ወርዋሪዎችም አዘጋጁ፤
ከአምስት ቀን በኋላ የካህናት አለቃው ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እነርሱም ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ ቀርበው ጳውሎስን ከሰሱ፤