ሐዋርያት ሥራ 22:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ብርሃኑን አዩ እንጂ እርሱ ሲያነጋግረኝ ድምፁን አልሰሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ ጋራ የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የሚናገረኝን የርሱን ድምፅ በትክክል አልሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ፈሩ፤ የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ ግን አልሰሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብረውኝ የነበሩትም መብረቁን አይተው ደነገጡ፤ ነገር ግን ይናገረኝ የነበረውን ቃል አልሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ፈሩ፥ የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ ግን አልሰሙም። |
ንጉሥ ሆይ! በመንገድ ሳለሁ ልክ እኩለ ቀን ሲሆን ከፀሐይ ብርሃን የሚበልጥ ብርሃን አየሁ፤ ይህም ብርሃን በእኔና ከእኔ ጋር በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ከሰማይ አበራ።