ሐዋርያት ሥራ 22:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቶ አለቃው ይህን በሰማ ጊዜ ወደ አዛዡ ሄደና “ምን ልታደርግ ነው? ይህ ሰው እኮ የሮም ዜጋ ነው!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመቶ አለቃውም ይህን ሲሰማ፣ ወደ ጦር አዛዡ ቀርቦ፣ “ምን እያደረግህ እንደ ሆነ ዐውቀሃል? ሰውየው እኮ ሮማዊ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቶ አለቃውም በሰማ ጊዜ ወደ ሻለቃው ቀርቦ “ይህ ሰው ሮማዊ ነውና ታደርገው ዘንድ ካለህ ተጠበቅ፤” ብሎ ነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቶ አለቃውም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ሻለቃው ሄደና፥ “ይህ ሰው ሮማዊ ነው፥ የምታደርገውን ዕወቅ” ብሎ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቶ አለቃውም በሰማ ጊዜ ወደ ሻለቃው ቀርቦ፦ ይህ ሰው ሮማዊ ነውና ታደርገው ዘንድ ካለህ ተጠበቅ ብሎ ነገረው። |
ነገር ግን በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲዘጋጁ ጳውሎስ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮም ዜግነት ያለውን ሰው ያለ ፍርድ ልትገርፉት ተፈቅዶላችኋልን?” አለው።
ስለዚህ እነዚያ ሊመረምሩት ተዘጋጅተው የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ከእርሱ ራቁ፤ አዛዡም የሮም ዜጋ የሆነውን ሰው በሰንሰለት ማሰሩን በተገነዘበ ጊዜ ፈራ።