ሐዋርያት ሥራ 21:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኛ የምንልህን አድርግ፤ በእኛ መካከል ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የምንልህን አድርግ። ስእለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ይህን የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ይህን የምልህን አድርግ፦ ብፅዐት ያላቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ይህን የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። |
ጳውሎስ ከወንድሞች ጋር ብዙ ቀኖች በቆሮንቶስ ከቈየ በኋላ ተሰናብቶአቸው ወደ ሶርያ ሄደ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ነገር ግን ስለት ስለ ነበረበት ከመሄዱ በፊት ክንክሪያ በሚባል ቦታ ራሱን ተላጨ።
ከአይሁድ ጋር ስሆን አይሁድን ለማዳን እንደ አይሁዳዊ ሆንኩ፤ እኔ ከሕግ በታች ባልሆንም እንኳ ከሕግ በታች ያሉትን ለማዳን ስል ከሕግ በታች እንዳሉት ሰዎች ሆንኩ።